የቅዱሳን አማላጅነት - ስለኛ መጸለይ ነው!
1. ከጌታችን (እግዚአብሔር) ወልድ ማስታረቅ የተለየ ነው፡፡
2. “… እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።” ያዕ 5፡16፡፡
3. ቅዱሳንም ሰዎች ይጸልዩላቸው ዘንድ ጠይቀዋል፡፡ “በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጌታ ቃል እንዲሮጥ በእናንተም ዘንድ
ደግሞ እንደሚሆን እንዲከበር፥ እምነትም ለሁሉ ስለማይሆን ከዓመፀኞችና ከክፉዎች ሰዎች እንድንድን ስለ እኛ ጸልዩ።”
2ኛ ተሰ 3፡1፡፡
4. “ጸልዩልን…” እብ 13፡18፡፡
5. “በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤
ደግሞ የወንጌልን ምሥጢር በግልጥ እንዳስታውቅ አፌን በመክፈት ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ስለ እኔ ለምኑ፡፡” ኤፌ 6፡18-19፡፡
6. ታዲያ እንደኛ ባለ መንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ ያሉትን ጸልዩልን ብለን የምንጠይቅ ከሆነ የዚህን ዓለም ውጊያና ፈተና
በድል ተወጥተው የፈጸሙትንና በገነት የሚገኙትን ቅዱሳን ጸልዩልን ብለን መጠየቅ የለብንም???
- “እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፡፡” እብ 11፡33
- “እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ
ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ።” ራእይ 3፡21
- “በእሳትም የተቀላቀለውን የብርጭቆ ባሕር የሚመስለውን አየሁ፥ በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቍጥር ላይ
ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ።” ራዕ 15፡2፡፡
እግዚአብሔር የቅዱሳንን አማላጅነት እንድንጠቀም ጠይቆናል !
1. አብርሃምና ንጉሥ አቤሜሌክ፡ ር - “አሁንም የሰውዬውን ሚስት መልስ ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፥
ትድናለህም። ባትመልሳት ግን አንተ እንድትሞት ለአንተ የሆነውም ሁሉ እንዲሞት በእርግጥ እወቅ።” ዘፍጥ 20፡7፡፡
2. ኢዮብና ሦስቱ ጓደኞቹ፡- “እግዚአብሔርም ይህን ቃል ለኢዮብ ከተናገረ በኋላ እግዚአብሔር ቴማናዊውን ኤልፋዝን፦
እንደ ባሪያዬ እንደ ኢዮብ ቅንን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና ቍጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ ላይ ነድዶአል።
አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ ባሪያዬ ወደ ኢዮብ ዘንድ ሂዱ፥ የሚቃጠልንም
መሥዋዕት ስለ ራሳችሁ አሳርጉ ባሪያዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፥ እኔም እንደ ስንፍናችሁ እንዳላደርግባችሁ ፊቱን
እቀበላለሁ እንደ ባሪያዬ እንደ ኢዮብ ቅን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና።” ኢዮ 42፡7-8፡፡
3. በሁለቱም ክስተቶች እግዚአብሔር ራሱ የበደሉትን ሰዎች በቀጥታ ተናግሯቸዋል፡ - የኃጢአታቸውንም ሥርየት
በቀጥታ አልሰጣቸውም፡፡ የኃጢአታቸውን ሥርየት እንዲያገኙ ቅዱሳኑ ይጸልዩላቸው ዘንድ ቅድመ ሁኔታ
አስቀመጠላቸው፣ ቅዱሳኑም በሰው ሁሉ ፊት በሁለቱም በደለኞች ፊታቸው ክብር እንዲደገኙ አድርጓል፡፡
4. አብርሃምና ስለ ሰዶም ያቀረበው ምልጃ፡ -
- “እግዚአብሔርም አለ፦ እኔ የማደርገውን ከአብርሃም እሰውራለሁን?” ዘፍጥ 18፡17፡፡
- “አብርሃምም ቀረበ አለም። በውኑ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ታጠፋለህን? ሀምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ
ሁሉን ታጠፋለህን? ከተማይቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ ሀምሳ ጻድቃን አትምርምን? ይህ ከአንተ ይራቅ ጻድቁን ከኃጢአተኛ
ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን
ፍርድ አይፈርድምን? እግዚአብሔርም፦ በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ ሀምሳ ጻድቃን ባገኝ ስፍራውን ሁሉ ስለ እነርሱ እምራለሁ
አለ። አብርሃምም መለሰ አለም። እኔ አፈርና አመድ ስሆን ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ እነሆ አንድ ጊዜ ጀመርሁ ከሀምሳው ጻድቃን
አምስት ቢጐድሉ ከተማይቱን ሁሉ በአምስቱ ምክንያት ታጠፋለህን? ከዚያ አርባ አምስት ባገኝ አላጠፋትም አለ። ደግሞም
ተናገረው፥ እንዲህም አለ፦ ምናልባት ከዚያ አርባ ቢገኙሳ? እርሱም፦ ለአርባው ስል አላደርገውም አለ። እርሱም፦ ጌታዬ አይቆጣ
እኔም እናገራለሁ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ? አለ። እርሱም ከዚያ ሰላሳ ባገኝ አላጠፋም አለ። ደግሞም፦ እነሆ፥ ከጌታዬ ጋር
እናገር ዘንድ አንድ ጊዜ ጀመርሁ ምናልባት ከዚያ ሀያ ቢገኙሳ? አለ። እርሱም፦ ከዚያ ሀያ ቢገኙ ስለ ሀያው አላደርገውም አለ።
እርሱም፦ እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ ምናልባት ከዚያ አሥር ቢገኙሳ? አለ። እርሱም፦ ስለ አሥሩ አላጠፋትም
አለ።” ዘፍጥ 18፡23-32፡፡
ይቀጥላል...........
ይህንን ሃሳብ በአገናዛቢነት ብንመለከትስ። http://bible-question-and-answer.blogspot.com/2012/02/blog-post.html
ReplyDelete