የምስጋና ቅኔ በፊትህ ለማቅረብ፤
ማለፍ ነበረብን አስፈሪውን ወጀብ።
አንተ ብትረዳን አንተ ብታግዘን፤
ታይተው ነበረ ጠፉ ከመባል አዳንከን።
የትኛው ግብራችን ከሞት አተረፈን፤
ቸርነትህ እንጂ በህይወት ያቆየን።
መንገድ ሰተን ወጥተን ተጋልጠን ለአደጋ፤
ማእበል ወጀብ ገጥሞን እጅግ የሚያሰጋ።
ድንግል ከለለችን ግርማ ሞገስ ሆና፤
ስሟን ጠርተን አንዴም አላፈርንምና።
በመከራው ሰዓት በዚያ ጭንቅ ቦታ፤
ስምሽን ጠረን ድንግል ስምህን ጠራን ጌታ።
ወስብአት ለእግዚአብሄር
No comments:
Post a Comment