Tuesday, 21 June 2011

የጥፋት ሃይማኖት

ሃይማኖት በጠባዩ ከፍ ያለ የሞራል ብቃትን የሚያጠይቅ ነው፡፡ በእምነቶች ታሪክ ውስጥ «ብቃት»የሚለው ቃል በተደጋጋሚ የሚነሣ እና ምእመናኑ ሁሉ የሚመኙት ነገር ነው፡፡ እነዚህ ለብቃት የደረሱየየእምነቱ ሰዎች ደግሞ ራሳቸውን ከማሸነፍ አልፈው ዓለምን በፍቅር እና በደግነት ያሸነፉ ናቸው፡፡አንዳንዶቹም ከሰዎችም በላይ ለእንስሳቱ እንኳን ሳይቀር በመራራት ለምነዋል፣ የደግነት ሥራ ሠርተዋል፤ከዚያም አልፎ መከራ ተቀብለዋል፡፡
ሃይማኖት ጸሎትን፣ አምልኮን፣ ደግ ሥራን እና ትምህርትን መሠረት አድርጎ የሰዎችን አስተሳሰብን እናአመለካከትን መለወጥን የሚያመለክት ኃይል ነው፡፡ በሃይማኖት ምክንያት ተደረጉ የሚባሉ ጦርነቶችንእንኳን ጠለቅ እያልን ስናያቸው ሃይማኖትን እንደ መሣሪያ ለመጠቀም በፈለጉ አካላት የተደረጉ እንጂየማይማኖቶችን ድንጋጌ ተከትለው የተደረጉ ሆነው አናገኛቸውም፡፡
አሁን አሁን በዓለማችንም ሆነ በሀገራችን ሃይማኖትን በጥፋት የማካሄድ አዝማሚያዎች እየታዩእየተከናወኑም ነው፡፡ በመግደል፣ ቤተ አምልኮን በማቃጠል፤ ሴቶችን በመድፈር፣ በግዳጅ በማግባት፣መብትን በመንሣት፣ በማስጨነቅ እና በሌላው ቤተ እምነት ላይ ወረራ በማካሄድ ለማሳመን መሞከርእየታየ ነው፡፡
ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት በበሻሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን እና በአካባቢው የነበሩክርስቲያኖች እምነታችንን በግድ እንጭናለን በሚሉ ጽንፈኛ «ሙስሊሞች» መታረዳቸው እንኳንከክርስቲያኖች ከሙስሊም ወገኖች እንኳን ከባድ ተቃውሞ ቀርቦበት ነበር፡፡
ከአምስት ዓመታት በኋላ ደግሞ ከሕግም፣ ከታሪክም፣ ከዘመንም የማይማሩ ጽንፈኞች የፕሮቴስታንትአብያተ ጸሎትን እያቃጠሉ እስልምናን በግድ መቀበል አለባችሁ ማለት መጀመራቸውን እየሰማን፤ሰምተንም እያዘንን ነው፡፡
ይህንን የመሰለው ተግባር ማንም ፈጸመው ማንም፤ በማንም ላይ ተፈጸመ በማን ኢትዮጵያ እናኢትዮጵያውያን ፈጽመው ሊቀበሉት እና ዝም ሊሉት የሚገባ ግን አይደለም፡፡
ሰዎች እኛ መልካም ነው ብለን ባመንነው መንገድ እንዲጓዙ መመኘት፣ ለዚህም መትጋት፣ ማስተማር፣በሞራል እና በበጎ ሥራ ልቆ በመገኘት መማረክ፣ ያኛው ተሳስቷል ብሎ ማሰብ እና በሠለጠነ መልኩስሕተት የሚባለውን መግለጥ የቀናዒ ኅሊና ባለቤት መገለጫዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን «ወደድክምጠላህም የግድ የኔን እምነት ብቻ ትቀበላለህ፣ እምቢ ካልክ ትሞታለህ» በሚል አስተሳሰብ መሥራትከሰውነት ተራ አውጥቶ ወደ ሰይጣንነት የሚያደርስ የሲኦል መንገድ ነው፡፡
ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ከሦስት ነገሮች ሊመነጭ ይችላል፡፡
የመጀመርያው ሃሳብን ለማስረዳት እና ለማሳመን ዐቅም ሲያጥር ነው፡፡ አንድ ሰው፣ ቡድን፣ተቋም ወይንም ማኅበረሰብ እርሱ በጎ ነው ብሎ የተቀበለውን አስተሳሰብ፣ አመለካከት ወይንም እምነትአስረድቶ፣ አብራርቶ እና በሚገባ አቅርቦ ማሳመን ሲያቅተው የሰነፍ ዱላውን መሠንዘር ይጀምራል፡፡
ይህ ሁኔታ አመለካከት ወይንም አስተሳሰብ እንኳን ሌላውን ሊያሳምን ይቅርና የያዘውም ሰው በሚገባእንዳልገባው ያሳያል፡፡ እርሱም ራሱ ጭፍን ስለሆነ ወይንም ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል እልክ እንደሚከተለው ያመለክታል፡፡ የሃሳብ ክርክር ከተነሣ ልሸነፍ እችላለሁ፣ ሊያሳምነኝ ይችል ይሆናል ብሎየሚሰጋ አካል ከሃሳብ ክርክር ይልቅ የመሣርያውን ክርክር ይመርጣል፡፡ ምክንያቱም የመሣርያ ክርከርከሃሳብ ክርክር ይልቅ ቀላል ነውና፡፡
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ከውጤቱ ይልቅ ድርጊቱን ብቻ በማየት የሚመጣም ነው፡ በዓለምላይ ያሉ እምነቶች ሁሉ በአንድ ዓላማ ይስማማሉ፡፡ ሰውን ከክፉው አውጥተው ወደ በጎው ዓለምመውሰድ ዓላማቸው ነው፡፡ ይህም ማለት ዋና አጀንዳቸው ሰው ነው ማለት ነው፡፡ ታድያ ልታሳምነው እናልታድነው የሚገባውን ሰው እንዴት ገድለህ ታሳምነዋለህ? ከገደሉ በኋላ ማሳመንስ አለ?
ይህ ዓይነቱ ሰይጣናዊ ሥራ የሚሠራው የመሰላቸውን ነገር ማድረጋቸውን እንጂ የሚያመጡትን ውጤትምንነት በማያስቡ ጨለምተኞች ነው፡፡ ጨለምተኞች ለራሳቸው ጀብዱ እንጂ ለሚያስከትሉት ውጤትአይጨነቁም፡፡ የፈለጉትን እና መልካም መስሎ የታያቸውን ማድረጋቸውን እንጂ በድርጊታቸው ምንለውጥ እንዳመጡ ማሰብ አይፈልጉምም፤ አይችሉምም፡፡
ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ ከእምነት ውስጥ «ሰውነት» ሲጎድል የሚከሰት ነው፡፡ ማንኛውምአማኝ አማኝ ከመሆኑ በፊት ሰው ነበር፡፡ ለማመን የበቃውም ሰው በመሆኑ ነው፡፡ ግኡዝ ወይንም እንስሳቢሆን ኖሮ አያምንም ነበር፡፡ አማኝ መሆኑ ሰው በመሆኑ ሊኖሩት የሚገቡትን በጎ ነገሮች ይበልጥያጠናክራል፤ ሌሎች በጎ ነገሮችንም ይጨም ርባቸዋል፤ ሰው በመሆኑ የሚከሰትበትን ድካምም በእምነትያሸንፈዋል፡፡
አማኝነት ሰው መሆንን ካጠፋ እና አውሬነትን ከተካ ግን ይህ አማኝነት አይሆንም፡፡ ምክንያቱም አራዊትሃይማኖት የላቸውም፤ ሊኖራቸውም አይችልምና፡፡ ለምሳሌ ለሰዎች ማዘን ሰው የመሆን ጠባይ ነው፡፡ለዚህም ነው በሁሉም ዓይነት ማኅበረሰቦች ውስጥ ሰዎች ሲሞቱ በልዩ ሁኔታ የሚታዘንላቸው፡፡ ይህንንጠባይ እምነት ያጠነክረዋል፤ በሚገባ ጎልቶ ወጥቶ ለምግባር እንዲበቃ ያደርገዋል እንጂ ሊያጠፋውአይገባም፡፡
ሰውን በመግደል፣ የሰውን ቤተ እምነት በማቃጠል፣ የሰውን ክብር በመንካት፣ መብቱን በመገደብ፣በእምነቱ ምክንያት አድልዎ በማድረግ፣ በማስጨነቅ እና አካላዊ ጉዳት በማድረስ ለማሳመን ወይንምለማጥፋት መጣር በምንም መልኩ የአማኝ ሰው መገለጫ ሊሆን አይችልም፡፡ እምነት ሰውነትንአይደፈጥጥምና፡፡
አሁን አሁን እምነታቸው ሰውነታቸውን ያጠፋባቸው፤ በእምነት ኃይል ከሰውነት ወደ መልአክነትይሸጋገራሉ ሲባሉ ጭራሽ ወደ አውሬነት የወረዱ አካላትን እያየን ነው፡፡ የአውሬን ሥራ ለመሥራትእምነት ምን ያደርጋል) እምነትኮ አውሬነትን አሸንፎ፣ ሰውነትን አልዕሎ መልአክነትን ገንዘብ ለማድረግነው፡፡
ሰውን በእምነቱ ምክንያት መግደል፤ ገንዘቡን መስረቅ፣ ሰውን በእምነቱ ምክንያት መጨቆን፤ ሴትንበእምነቷ ምክንያት መድፈር፤ ድኻን በእምነቱ ምክንያት አለ መርዳት፣ የሰውን ቤት በእምነቱ ምክንያትማቃጠል እንዴት ሃይማኖት ሊሆን ይችላል? «መግደል፣ መስረቅ፣ መድፈር፣ አድልዎ፣ ማቃጠል»እነዚህን ድል መንሣት የተሣነው እምነት እንዴት እምነት ይሆናል?
ይህ ሰይጣናዊ ተግባር በማንም ተፈጸመ በማን፣ በማንም ላይ ተፈጸመ በማንም ላይ በሁሉም የሰው ዘርሊወገዝ የሚገባው ድርጊት ነው፡፡ ምክንያቱም ከሰውነትም የወረደ ድርጊት ስለሆነ፡፡ ይህ ዓይነቱ ድርጊትሰዎችን አይወክልም፣ አማኞችንማ ጭራሽ አይመለከትም፡፡ ይህ ዓይነቱን ሰይጣናዊ ሥራ እምነት አለኝየሚል ሁሉ ሊያወግዘው፣ ሊጸየፈው እና ሊያነውረው የሚገባ ነው፡፡
ትናንት በኦርቶዶክሳውያን ላይ፣ ዛሬ ደግሞ በፕሮቴስታንት ወገኖቻችን ላይ ተፈጸመ፡፡ ነገ በሌሎች ላይለሦስተኛ ጊዜ እስኪፈጸም መጠበቅ የለብንም፡፡ በኔ አልተፈጸመም፣ እኔንም አይመለከትም ልንልምአንችልም፡፡ ይህ ዓይነቱ ድርጊት በአንድ እምነት ላይ የሚፈጸም ሳይሆን «በሰውነት» ሰው በመሆን ላይየሚፈጸም ወንጀል ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ይህንን የፈጸሙት ወገኖች እንኳን ይህንኑ አስተሳሰባቸውንበአስተሳሰብ ልዕልና እንዲለውጡ እንጂ በገጀራ እንዲለውጡ ማናችንም አንፈልግም፡፡
የድኅነት እንጂ የጥፋት ሃይማኖት ሊኖር አይችልምና፡፡

No comments:

Post a Comment