Wednesday, 11 January 2012

መንፈሳዊነት ጠገግ ወይስ ሕይወት?

በዓለም ላይ በሃይማኖት መንገድ አያሌ የጽድቅ ሥራዎች ተሠርተዋል፤ በተቃራኒውም በሃይማሽፋን አያሌ ግፎች ተሠርተዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ሃይማኖትን የሕይወት መንገዳቸው ሳይሆንየሕይወት ጠገጋቸው በማድረጋቸው ምክንያት፡፡ የእምነቱን ሕግ እና ሥርዓት ለማክበር ሳይሆንበእምነቱ ስም ሊገኙ የሚችሉ ጥቅሞችን ለማነፍነፍ በመጠጋ ታቸው የተነሣ፡፡ ለፖለቲካ፣ለኢኮኖሚ እና ለሥልጣን ዓላማቸው ማስፈጸሚያ ሲሉ ሃይማኖትን ተጠግተው ለሃይማኖታቸውሳይሆን በሃይማኖታቸው ይጠቀማሉ፡፡

ይህ ሲሆን ደግሞ ሃይማኖት ዓላማውን ይስታል፡፡ የሃይማኖት ዋናው ዓላማ በሃይማኖት መመርያመሠረት ለሰማያዊ ዋጋ የሚያበቃ መልካም ነገርን በምድር ላይ መፈጸም ነው፡፡ ሃይማኖት የፈጣሪንመንግሥት ይሰብካል፣ ፖለቲካ ደግሞ ምድራዊ መንግሥት፣ ሃይማኖት ሰማያዊ ትርፍን ይሰብካል፣ንግድ ደግሞ ምድራዊ ትርፍ፣ ሃይማኖት ሰማያዊ ሹመትን ይሻል፣ ሥልጣን ደግሞ ምድራዊ፡፡
ሃይማኖት ምድራዊ ሕይወታችንን ሲቃኘው ኑሯችን መንፈሳዊም ሥጋዊም ጤናው የተጠበቀይሆናል፡፡ ንግድ፣ ፖለቲካ፣ ዘር እና ሥልጣን ሃይማኖትን ሲቃኘው ግን ሃይማኖት ከሰማያዊው ግቡጋር ይቆራረጣል፡፡
በተለይም ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በልዩ ልዩ እምነት የሚያምኑ ዜጎች በአንድ ላይ ተግባብተውእና ተገናዝበው በሚኖሩባት ሀገር ሃይማኖት ሰማያዊውን ዓላማ ለቅቆ ምድራዊ መሆን ከጀመረየፍቅር እና የአንድነት ማሠርያነቱ ላልቶ የጠብ እና የጦርነት መንሥኤ ሊሆን ይችላል፡፡
ሃይማኖት መሥመሩን ለቅቆ ከማዋሐጃነት ወደ መከፋፈያ መሣርያነት የሚያመራው የሕዝቦችግንኙነት ሃይማኖትን ብቻ መሠረት እያደረገ መጓዝ ሲጀምር ነው፡፡ በሕዝብ ግንኙነቶች ውስጥሃይማኖትን ብቻ መሠረት የሚያደርጉ ግንኙነቶች አሉ፡፡ እነዚህ ግንኙነቶች በማኅበረሰቡ መካከልያለውን ተዛምዶ የማያበላሹ እና በየእምነት መጻሕፍቱም የተደነገጉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የጋብቻግንኙነቶች አልፎ አልፎ ካልሆነ በቀር የሃይማኖት ቤተሰብነትን መሠረት ያደርጋሉ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሃይማኖትን የግድ መሠረት ማድረግ የሌለባቸው ማኅበራዊ ግንኙነቶችም አሉ፡፡የፖለቲካ፣ የንግድ፣ የአካባቢ፣ የርዳታ፣ ወዘተ ዓይነት ግንኙነቶች፡፡ እነዚህ ግንኙነቶች ተመሳሳይአለመካከቶችን፣ ውሎችን፣ የሀገር ሕጎችን እና ሰብአዊነቶችን መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡
አንድ ከርስቲያን የምነግደው ከክርስቲያኑ ጋር ብቻ ነው ካለ፣ አንድ ሙስሊምም በዚሁ መንገድከተጓዘ፣ በአንድ አካባቢ ለመሥፈር ወይንም መኖርያን ለመሥራት አካባቢው የክርስቲያን ወይንምየሙስሊም ተብሎ ከተከፈለ፣ በአንድ መሥሪያ ቤት ለመቀጠር የኃላፊዎቹን ወይንም የባለቤቶቹንእምነት ማመን ዋና መመዘኛ ከሆነ፣ ርዳታ ለማግኘት የረጅዎቹን እምነት መቀበል አስገዳጅ ቅድመሁኔታ ከተደረገ ሀገር እንደ ሀገር መኖር ይከብዳታል፡፡
እንዲህ እንደኛ ልዩ ልዩ እምነቶችን የሚከተሉ ሕዝቦች ያሉባት ሀገር ሕዝቦቿ በሰላም እና በጤናመኖር እንዲችሉ ሦስት ነገሮች ያስፈልጓታል፡፡ መተዋወቅ፣ መገናዘብ እና ከድምሩ በላይ ማሰብ፡፡
ለመሆኑ ከእኔ የተለየ እምነት ያለው ወገኔ ምንድን ነው የሚያምነው? ለምን? ከኔ ልዩነቱ እናአንድነቱ ምንድን ነው? የሚጠላው እና የሚወድደው ምንድን ነው? እኔ እና እርሱ ሳንጋጭምሳንዋዋጥም እንዴት ተግባብተን ልንኖር እንችላለን? በሚሉት ጉዳዮች ላይ አንዱ ስለ ሌላው ግንዛቤእንዲኖረው ማድረጉን ነው መተዋወቅ የምንለው፡፡
አንዳንድ ጊዜ ስለሌሎች የሰማናቸው እና ያወቅን የመሰሉን ነገሮች የተዛቡ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡በጠላትነት የምንተያየውም በተነገሩን የተዛቡ መረጃዎች ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ የማያምኑትንእንደሚያምኑ፣ የማይቀበሉትን እንደሚቀበሉ፣ የማይደግፉትንም እንደ ሚደግፉ እያደረግንየሰማናቸው እና ያነበብናቸው ነገሮች ይኖራሉ፡፡ ምናልባትም አንዳችን ስለሌላችን ባለማወቃችንየተነሣ የሌሎችን መብቶች ልንደፈጥጥም እንችላለን፡፡ በቃላት አጠቃቀማችንም እንስታለን፡፡
መተዋወቅ እነዚህን ሁሉ ነው የሚፈታው፡፡ ብዙ ጊዜ መተዋወቅን ከመሳሳብ እና እምነትንከመለወጥ አንፃር ስለምናስበው መገፋፋት በመካከል ይሰፍናል፡፡ ሰው ሌላውን ማወቅ ያለበትእምነቱን እና አመለካከቱን ለመለወጥ ብቻ አይደለም፡፡ የራስን አመለካከት መለወጥ እና ስለሌላውያለንን አመለካከት መለወጥ ይለያያሉ፡፡
መገናዘብ የምንለው ምናልባትም ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ይገኝ የነበረ አሁን ግን እየተዳከመ የሄደ በጎጠባይ ይመስለኛል፡፡ አንድን እምነት ዐውቆ፣ ያንን አማኝ ላለማስቆጣት እና ማኅበራዊ ግንኙነትንላለማበላሸት ተጠንቅቆ፣ ነገር ግን መተጋገዝ እና አብሮ መኖር ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያውያንሙስሊሞች ቤተ ክርስቲያን ለሚሠሩ ክርስቲያን ወገኖቻቸው ርዳታ ሲሰጡ እስልምና አይጠቅምምብለው የራሳቸውን ትተው፣ ወይንም ክርስትና ከኛ ይሻላል ብለው በክርስትና አምነው አይደለም፡፡ለክርስቲያን ወገኖቻችን ቤተ ክርስቲያን ሊኖራቸው ይገባል ብለው እንጂ፡፡ ክርስቲያኖችምእንዲሁ፡፡ መገናዘብ ማለት ይሄ ነው፡፡
በማኅበራዊ ግንኙነቶቻችን ውስጥ ይህንኑ ነው የምናየው፡፡ በሙስሊሞች በዓል እንኳን አደረሳችሁለማለት ክርስቲያኖች በቤታቸው ሲገኙ ሙስሊም ወገኖቻቸው ለምግባቸው ተጠንቅቀው ነው፡፡ይገናዘባሉና፡፡ ለእነርሱ ተብሎ የተዘጋጀውን የሚያቀርቡት የክርስቲያኖቹን ፍላጎት ተገንዝበው ነው፡፡
ሦስተኛው ከድምሩ በላይ ማሰብ መቻል ነው፡፡ ከእኛ ከአማኞቹ በላይ የሆነች ኢትዮጵያ የምትባልሀገር አለች፡፡ ሁላችንም እንደልባችን ልንሆን የምንችለው ይህቺ ሀገር እንደ ሀገር ስትኖር ነው፡፡እናም ይህቺን ሀገር እንደ ሀገር ለማኖር ስንል የምንከፍለው ሰማዕትነትም አለ፡፡ እኛ የየራሳችንንእምነት ብቻ እየተመለከትን በምናደርገው ሥጋዊ ፉክክር ይህቺ ሀገር እንዳትጎዳ የመጠንቀቅግዴታም አለብን፡፡ ስለ ክርስትና ቅርሶች፣ ስለ እስልምናም ታሪካዊ ቦታዎች ስናስብ ስለ ኢትዮጵያሀብቶች ማሰብ አለብን፡፡ ከወዲህ ማዶ እኛ ድንበሩን በገፋነው መጠን ከወዲያ ማዶም የሚገፋመኖሩን መርሳት የለብንም፡፡
አለቃ ገብረ ሐና ቤት ወይዘሮ ማዘንጊያ በሌሉበት አንዲት ሴት የስድስት ወር ልጇን ይዛትመጣለች፡፡ የመጣችበት ምክንያት አልታወቀም፡፡ በድንገት ወይዘሮ ማዘንጊያ ሲገቡ ሴቲቱ ደንግጣየራሷን ልጅ ትታ የማዘንጊያን ልጅ ይዛ ትሮጣለች፡፡ ማዘንጊያ አለቃ የባለጉ መስሏቸው ተናደዱ፡፡ወዲያው ልጁን አነሡና እሳት ውስጥ ሊጨምሩት ወደ ምድጃው ሲሄዱ አለቃ «ተይ ማዘንጊያእዚያም ቤት እሳት አለ» አሏቸው ይባላል፡፡
እዚህ ቤት አንዳች ነገር ሲደረግ እዚያም ቤት ሊደረግ እንደሚችል ማሰብ ነው፡፡ እዚህ አካባቢለምናቃጥላት ቤተ ክርስቲያን ወይንም መስጊድ በሌላ አካባቢ ዋጋውን ልንከፍልበት እንችልይሆናል፡፡ እዚህ ሙስሊሞች አንሰው ክርስቲያኖች ስለበዙ የምንጨቁን ከሆነ እዚያ ክርስቲያኖችአንሰው ሙስሊሞች በሚበዙበት ቦታ ደግሞ ተመሳሳዩ እንዲፈጸም እያሳሰብን ነው ማለት ነው፡፡አለቃ እንዳሉት እዚያም ቤት እሳት አለና፡፡
አሁን አሁን በዚህች ሀገር ከሚያሳስቡኝ ነገሮች አንዱ በሃይማኖት ንጣሌ የማሰብ አመለካከት ነው፡፡በሃይማኖት ንጣሌ የማሰብ አመለካከት ማንኛውንም ነገር በሃይማኖት መነጽር ብቻ የማየትአስተሳሰብ ነው፡፡ አክስዮን ለመመሥረት ተመሳሳይ ሃይማኖት፣ ገንዘብ በባንክ ለማስቀመጥተመሳሳይ ሃይማኖት፣ አንድ አካባቢ ለመኖር ተመሳሳይ ሃይማኖት፣ አንድን ነገር በጅምላ ወይንምበርካሽ ለማግኘት ተመሳሳይ ሃይማኖት፣ ርዳታ ለማግኘት ተመሳሳይ ሃይማኖት፣ ሥራ ለማግኘትተመሳሳይ ሃይማኖት መጠየቅ እየተጀመረ ነው፡፡
ፈጣሪያቸውን አምነው፣ እርሱ የፈቀደውን አድርገው የርሱን መንግሥት ለመውረስ የተሰባሰቡወገኖች ዓላማቸውን ቀይረው የአማኙን ስብስብ እንደ አማራጭ ገበያ፣ እንደ ደንበኛ ማፍሪያ፣ እንደገንዘብ መሰብሰቢያ፣ ለሥልጣን እንደ መሸጋገርያ፣ የድምጽ ማግኛ፣ የርዳታ እህል መለመኛ ካደረጉትበዚህች ሀገር ንጥያ እየተባባሰ ነው ማለት ነው፡፡
በተለይም ቢቻል ከአባቶቻችን የተሻለ እንሠራለን፣ ባይቻልም አባቶቻችንን እናበረታለን ብለውየሚሰባሰቡ ወጣት መንፈሳውያን ለጽድቅ የተሰባሰቡባቸውን ማኅበራት ወደ ንግድ «ኢምፓየር»የሚቀይሯቸው ከሆነ፣ በመንፈሳዊ ዓላማ እና በሰማያዊ ግብ ያሰባሰቧቸውን አባላት ከሰማይአውርደው በአክስዮን እና በካፒታል መዋጮ የሚያሰባስቧቸው ከሆነ፤ መንፈሳዊነቱ ሕይወትሳይሆን ጠገግ ሆኗል ማለት ነው፡፡
በመንፈሳውያን መካከል ሊኖር የሚገባው ግንኙነት መንፈሳዊነትን ብቻ መሠረት ያደረገ መሆንአለበት፡፡ የሚሠሯቸውም ሥራዎች ዓላማቸው ጽድቅ መሆን አለባቸው፡፡ መንፈሳውያን በምድር ላይበሥጋ ሊጠቀሙ ሳይሆን ሊጠቅሙ ነው የሚመጡት፡፡ መንፈሳውያን በሃይማኖት የሚሰባሰቡትመክሊታቸውን ሊያተርፉ እንጂ አክስዮናቸውን ሊያተርፉ አይደለም፡፡
እስካሁን ድረስ በእምነት ስም የተነሡ ግጭቶች ራሳቸው እምነቶቹ የፈጠሯቸው አይደሉም፡፡እምነቶቹን ለግላዊ ጥቅማቸው ማዋል የሚፈልጉ አካላት የፈጠሯቸው እንጂ፡፡ እነዚህ ሰዎችየመጀመርያቸው ሥራ ደግሞ በእምነቶቹ ሰማያዊ ዓላማ ላይ ምድራዊ ዓላማ መጨመር ነው፡፡የግጭቱ መነሻም ይኼው ምድራዊ ዓላማ ይሆናል፡፡
እነዚህ እየታዩ ያለ ክስተቶች እኛው ኢትዮጵያውያን ማረም አለብን፡፡ አሁን የሚያስፈልገንየኦርቶዶክስ፣ የፕሮቴስታንት፣ የእስልምና፣ የይሆባ፣ ባንክ አይደለም፡፡ እጅግ ዘመናዊ የሆነየኢትዮጵያ ባንክ ነው፡፡ አሁን የሚያስፈልገን በሃይማኖት ስም የተመሠረተው የማኅበረ እገሌወይንም እገሌ የአክስዮን ማኅበር አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ የአክስዮን ማኅበር ነው፡፡ አሁንየሚያስፈልገን የሙስሊም ወይንም የክርስቲያን ሆስፒታል አይደለም፡፡ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታልነው፡፡
አሁን የሚያስፈልገን የሙስሊም ወይንም የክርስቲያን የርዳታ ድርጅት አይደለም፡፡ የተቀበለውንገንዘብ ለታለመለት ዓላማ የሚያውል የርዳታ ድርጅት ነው፡፡ አሁን የሚያስፈልገን የክርስቲያኖችወይንም የሙስሊሞች ሠፈር አይደለም፡፡ ተስማሚ የመኖርያ ሠፈር ነው፡፡
ይህ ጉዞ ኢትዮጵያውያንን ተነጣጥለን ብቻ የምናስብ፣ በአንድ ሀገር ከመኖራችን በቀር የመግባቢያሰነድ የሌለን ያደርገናል፡፡ ምናልባትም በንግድ እና በገንዘብ ምክንያት የሚመጡ ግጭቶችም ወደእምነቶች ውስጥ ገብተው እንዲያተራምሱ ዕድል ይከፍታል፡፡ እናም ሃይማኖትን ለጽድቅ እናለድኅነት እንጂ ለንግድ «ኢምፓየር» መገንቢያነት አንጠቀምበት፡፡

No comments:

Post a Comment